ላለፉት
20 ዓመታት ማህበረ ቅዱሳን ቅኝ ግዛት ከያዛቸው ሀገረ ስብከቶች መካከል አንዱ የሆነው የድሬደዋ ሀገረ ስብከት በማህበሩ
አመራሮችና አባላት ዘንድ እጅግ የከፋ መከፋፈልና መጣረስ የደረሰበት ሲሆን፥ ምንም እንኳ የዘገየ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ
ተቃውሞ በማህበሩ ላይ ሲደመጥ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ከሰሞኑ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከትና ሠራተኞች፥ የአድባራትና የገዳማት አለቆች፣ እንዲሁም የሥራ
አመራሮች በአንድነት፥ የማህበረ ቅዱሳንን እኩይ ተግባር በጽኑ በማውገዝ፥ የተቃውሞ አቋም መግለጫ በማውጣት ተፈራርመዋል፡፡ ለብጹዕ
አባታችን ለድሬደዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ለአቡነ ዳንኤልም አቅርበዋል፡፡ በማህበረ ቅዳሳን ጣልቃ ገብ እጅ ላይ ከወዲሁ እርምጃ እንደሚወሰድ ይጠበቃል፡፡
እናት ቤተክርስቲያናችን ዛሬ ላይ ማህበረ ቅዱሳን
በተባለ ስብስብ ዋጋ እየከፈለች ባለችበት ወቅት፥ በአንጻሩ ደግሞ ብጹዐን
አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናትና ቀሳውስት፣ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በአንድነት የማህበሩን እኩይ ግብር
በጽኑ በማውገዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ተሰገሰገው ላሉት የማህበሩ
ቦርቧሪ ኃይሎችን ክፉኛ ያሳሰበ መሆኑን፥ ዳንኤል ክብረት በገዛ ብሎጉ ላይ ብጹዕ አባታችን ፓትርያሪክ
አቡነ ማቲያስን ‹‹ሰይጣን››
በሚል ዘይቤ የስድብ ናዳ ማውረዱን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ዳንኤል በፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ላይ የስድብ ናዳ ያወረደባቸው፥ እርሱ
እንደሚለው “ፓትርያሪኩ የማህበሩን ዐውደ ርዕይ
አላሳገዱም”፥ ዐውደ ርዕዩን በኃላፊነት ደረጃ
ያገደው የኢግዝቪዥን ማዕከል አስተዳደር በማህተሙ ማረጋገጡ የሚታወቅ ነውና፡፡ ዳንኤል ግን ይሄን ሳያጣራ በወፍ በረረ ብጹዕ አባታችንን
በሰይጣን እየመሰለ በስድብ አፉ ወረደባቸው፡፡ ብጹዕ አባታችን በዳንኤል ክብረት የወፍ በረረ ስድብና የክፋት ድርጊት ክፉኛ ማዘናቸውን
የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ግልፍተኝነት ማህበሩ አመራሮችና ደጋፊዎች ላይ በስፋት የመታየቱ ምስጢር፥ “የብጹአን አባቶችና ሊቃውነተ ቤተክርስቲያን
ከመላው ምዕመናት ጋር በአንድነት የማህበሩን ሕቡዕ አጀንዳ በመቃወመቻው” ምክንያት በአመራሮች ዘንድ ታላቅ
ሽብርን በማስከተሉ እንደሆነ ይገመታል፡፡
ይህ ዓይነቱ ክፉን ከመልካሙ፣ ዓመጸኛውን ከጻድቁ፣ ውሸቱን ከእውነቱ
የመለየቱና “የቤትህ ቅንዓት ይበላኛል” እንዲል መጽሐፍ፥ ለቅድስት ቤተክርስቲያን የመቆሙ ሥራ ይበል የሚያሰኝ ነውና መላው ኦርቶዶክሳዊ
ከድሬደዋ ሀገረ ስብከት ጎን ይቆም ዘንድ አቤት እላለሁ!
ቸር ሰንብቱልኝ!
ምንጭ፥ የድሬደዋ ሀገረ ስብከት ሠራተኛ
ጫፏ ላይ መርዝ እንደታሰረባት ረዥም ሲባጎ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳንም በተመዘዘ ቁጥር መርዛማነቱ ይገለጣል፡፡
ReplyDeleteጥሩ ታዝበሃል ወዳጄ
DeleteTebareku
ReplyDeleteTebareku
ReplyDeleteአሜን ተባረክ አንተ ወንድም ኢዮብ፡፡ መልዕክት ያላችሁ በኢሜል አድራሻችን በመላክ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ትችላላችሁ፡፡
ReplyDelete