Friday, May 27, 2016

“ከጠበሉ ይቅደም ወንጌሉ” ደቀመዝሙር ከፍያለው ቱፋ


በቅርቡ በአሰበ ተፈሪ ጭሮ ከተማ፥ ዘማሪ ዲያቆን ከፍያለው ቱፋ 17 ከሚደርሱ ቅዱሳን ጋር በቤት ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል በመማማር ላይ እያሉ፥ በሐሰት ክስ የእግዚአብሔርን ቃል ለማስቆም በሞከሩ ግለሰቦች ምክንያት ከሚያዚያ 9-12 መታሰራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይህ በሆነ ማግስት አንስቶ፥ “ሐራ ዘተዋሕዶ” የተባለች የመናፍቃን ብሎግና መሰል የማቅ ጽንፈኛ አባላት “ነውር ሰርተው እንደታሰሩ” ለማስመሰል የሐሰት ፕሮፓጋዳ ማናፈሳቸውን ተከትሎ፥ በተወሰነ መልኩ ቢሆንም ቅዱሳንን ግራ ለማጋባት ቢዳክሩም አልተሳካላቸውም፡፡ ኧረ ለመሆኑ ሰሚ ከተገኘ ወንጌልን በየትኛውም ሥፍራ መመስከርና መስበክ፥ እንደ ነውር የሚያስከስና ቁጣ የሚያስነሳ ነውን? አይደለም! በርግጥ ወንጌል ተሰበከ ብለው አምባጓሮ የሚፈጥሩ ግለሰቦች፥ በየትኛውም ዘመንና ጊዜ ቤተክርስቲያናንን ሊወክሉ ከቶ አይገባም፡፡ ምክንያቱም፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” ብሎናልና (ማር 16፡-15)!


ደቀመዝሙር ከፍያለው ቱፋም በግራ በቀኝ የተናፈሱትን ወሬዎችን ተመልክቶ፥ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ወቅታዊ መልዕክት በዩቲዩብ ድኀረ-ገጽ ለቋል፡፡ እኛም መልዕክቱን እነሆ ብለናል፡፡ (ይህን መልዕክት በዩቲዩብ፣ በፌስብኩ እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ድኀረ-ገጾች ላይ ሼር በማድረግ ከወንጌል ጎን የቆማችሁ ቅዱሳን፥ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡ አጽንዖት ከተመልካች አንዱ!)

No comments:

Post a Comment