ክፍል አንድ፥
በዲያቆን
ይስማዕከ ይነግስ
በዚህ ዘመን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከሚረብሹ
እንግዳ አስተምህሮቶች መካከል አንዱ “ጽዮን - ማርያም ናት” የሚለው ኑፋቄ ነው፡፡ ይህን እንግዳ
ትምህርት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በነገረ መለኮት ትምህርተ ዘለቀ እውቀት በሌላቸው በደባትራኑና ቤተክርስቲያኗን ለፖለቲካ አጀንዳቸው
ሲሉ ሽፋን አድርገው በሕቡዕ በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ዘንድ በስፋት ሲነገር ይደመጣል፡፡ “ጽዮን - ማርያም ናት” የሚለው ፍልስፍና ከቅርብ ጊዜ
ወዲህ ቀስ በቀስ የብዙዎችን ልቡና እያሳወረ፥ የስህተት አስተምህሮ ምርኮኛ ሊያደርጋቸው ችሏል፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ለእኛ ልጆቿ
በመጻህፍቶቿ ያላት አስተምህሮ “ጽዮን - ማርያም ናት” የሚል ፍልስፍና አይደለም፡፡ በማስረጃዎች
እንመልከት፡-
1. “እምነ ጽዮን በሐ ቅድስት ቤተክርስቲያን
ሥርጉተ ስብሃት ... እንተ ክርስቶስ መሰረትኪ ጸሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ፡፡” የአማርኛ ትርጓሜው እንዲህ ይላል፡- “ክርስቶስ የመሰረተሸ የጽድቅ ጸሐይ የሚያበራብሽ ምስጋናን የተሸለምሽ እናታችን ጽዮን ቅድስት ቤተክርስቲያን
እንዴት ነሽ?” ምንጭ፡- (መጽሐፈ ዚቅ፣ ገጽ 73 ይመለከቷል)፡፡ በዚህ ክፍል የምንማረው “ጽዮን - ማርያም ናት” የሚል ሳይሆን፤ ይልቁንም በሐዋርያት
አስተምህሮ፣ በአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት መሰረት ጽዮን - ቤተክርስቲያን እንደሆነች ነው የሚነግረን፡፡ እንግዲህ
ማንን እንስማ ዘንድ ይገባናል?
2. “ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት
እንዝ ትበኪ ከመ ብእሲት” የአማርኛ ትርጓሜው እንዲህ ይለናል፡- “ዕዝራም ጽዮን ቅድስትን እንደሴት
ስታለቅስ አያት” ምንጭ፡- (መጽሐፈ
ዚቅ፣ ገጽ 72 ይመልከቱ)፡፡ በዚህ ምንባብም በተመሳሳይ መልኩ ጽዮንን *እንደ ሴት ስታለቅስ አየሁ* በማለት ጽዮን ስለተባለችዋ
ኢየሩሳሌም በሰውኛ ዘይቤ፥ ከተማዋ ምን ያህል በሐዘን ድባብ መወረሷን፥ ካህኑ ዕዝራ ሲገልጻት እንመለከታለን፡፡ ከዚህ በተረፈ “ጽዮን - ማርያም ናት” የሚልን ፍልስፍና አናስተውልም፡፡
3. “ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት
በረእየተ ብእስት ወሶበ ርእያ ኢኮነት ብእስተ አላ ሀገር ቅድስት” የአማርኛ ትርጓሜው እንዲህ ይለናል፡- “ዕዝራም ጽዮን ቅድስትን በሴት አምሳል (መልክ) አየሁ፡፡ ባያት ጊዜም ሴት አይደለችም የተቀደሰች
ሐገር ናት እንጂ፡፡” ምንጭ፡- (መጽሐፈ ዚቅ፣ ገጽ 73 ላይ ይመልከቱ)፡፡ በዚህ ምንባብ ካህኑ
ጽዮን የተባለችዋን ኢየሩሳሌምን በሴት አምሳል ወይንም መልክ በራዕይ እንዳያት ይነግረናል እንጂ አካላዊ ሴትን አለማየቱን በግላጭ
ያስረዳል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም “ኢኮነት ብእስቲ፥ ሴት አይደለችም” በማለት የተመለከተው ሐገር መሆኑን
ያስረግጣል እንጂ ፈጽሞ “ጽዮን - ማርያም ናት” የሚልን እንግዳ ኑፋቄ
አይሰብከንም፡፡
4. “አብርሂ አብርሂ ጽዮን ዕንቁ ዘጳዝዮን ዘኀረየኪ ሰሎሞን” የአማርኛ
ትርጓሜው እንዲህ ይነበባል፡- “ሰሎሞን የመረጠሸ የጳዝዮን ዕንቁ አብሪ አብሪ፡፡”
ምንጭ፡-(መጽሐፈ ዚቅ፣ ገጽ 73 ይመልከቱ)፡፡ ይህ ክፍል ከላይ እንደተመለከትነው ጽዮን ስለተባለችው ኢየሩሳሌም የሚተርክ ምንባብ
ነው እንጂ እንዳችስ እንኳ ደባትራኑ እንደሚሉት ጽዮን ማርያም ናት የሚል አይደለም፡፡
እንግዲህ እኛ “ቤተክርስቲያንን እንስማ ወይስ የሐሰት አስተማሪዎችን እንግዳ ኑፋቄ” እናድምጥ? ለተጨማሪ መረጃ፡- ኪዳነ ምህረት መጽሄት፣ ቁጥር 18፣ በእንተ
ጽዮን የሚለው ትምህርት ያንብቡ!
... ይቀጥላል ...
tebareku
ReplyDeleteጥሩ አያያዝ ነው በርቱልን፡፡ በዚህ ከቀጠላችሁ ብዙ ሥራ እንደምትሰሩ አልጠረጥርም፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ፡፡
ReplyDeleteየሕይወትን ራስ ክርስቶስን መጋረድ የተጀመረው ዛሬ አይደለ፡፡ የዓለም መድኀኒት ጌታችን ኢየሱስ ወዲዚህች ምድር በተዋህዶ ሥጋ ሲሆን አንስቶ በሔርዶስ እና በመዋለ ሥጋው ሳለ ደግሞ በፈሪሳውያኑና በሰዱቃውያን ዘንድ ተግዳሪት ተነስቶበታል፡፡ ዛሬም ዉሉደ ፈሪሳውያን ወሰዱቃውያን አንድ ጊዜ ጽዮን ማርያም ናት ሌላ ጊዜ ታቦተ ጽዮን ድንግል ናት በማለት ጌታችንን ይሸሽጉት ዘንድ ሲደክሙ እንመለከታለን፡፡
ReplyDeleteYenegere Mariyam tentenaw yiketelal, Wengielum gena yisebekal. Tebareku ke gonachu negn.
ReplyDeleteበፍጹም ጽዮን ማርያም እይደለችም…የእግ/ር ከተማ ናት…….በፍጹም……. ሰው ተራራ..ፍርስራሽ ፣እርሻ አለው እንዴ???
ReplyDelete፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹፹
ትንቢተ ኤርምያስ 26፡18
ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል ብሎ ተናገረ።
ትንቢተ ሚክያስ 3፡12
12 ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌምም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።
ትንቢተ ሚክያስ 3፡10
10 ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ።
ሰቆቃው ኤርምያስ 4፡11
እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፥ ጽኑ ቍጣውን አፍስሶአል፤ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፥ መሠረትዋንም በላች።
መዝሙረ ዳዊት 48
1 እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።
2 በሰሜን ወገን በመልካም ስፍራ የቆመ የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው፤ እርሱም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነው።
ትንቢተ ኢሳይያስ 33፡14
14 በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፤ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከ
tebarek, Tsega yibzaleh
DeleteWow አፍርጠው እንዲህ!
ReplyDeletetebareku
ReplyDelete