ዲያቆን ደቀመዝሙር ከፍያለው ቱፋ ‹‹መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅተህ፥ ሰዎችን ሰብሰበሃል›› በሚል ተቃውሞ ክስ ተመስርቶበት፥
ከሰሞኑ 18 ከሚደርሱ ቅዱሳን ጋር መታሰሩን ሐራ ዘተዋህዶ መዘገቧ የሚታወቅ ነው፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ደቀመዝሙር ከፍያለው
ቱፋ የተከሰሰበት ክስ ፍሬ ከርስኪ መሆኑን ተረድቶ፥ ትላንት ማለትም 12/08/2008 ዓ/ም በአንድ ሺህ ብር ዋስ ፍርድ ቤቱ ሊለቀው
ችሏል፡፡ ፍርድ ቤቱም አክሎም “የማንንም ሃይማኖት መስደብ፣ መንቀፍና መዝለፍ በሕግ ፈጽሞ የተከለከለ
ነው፤ ደግሞም ማንም ሰው ያማነበትን እውነት መመስከርና መስበክ እንደሚችል” ገልጿል፡፡ በቦታው ላይ ፖሊስ ደርሶ
ነገሩን ባይቆጣጠር ኖሮ ደም በማፍሰስ የሚያምነው ማህበሩ፥ የወንድሞችንና የእህቶችን ደም ከማፍሰስ እንደማይቦዝን የታወቀ ነው፡፡
ኽረ ለመሆኑ ለሃይማኖት የተደባደበ ሐዋርያ ማን ነው?
አሁን አሁን በእናት ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ባሉ አንዳንድ ጽንፈኛ ግለሰቦች ምክንያት ወንድሞች በጋራ ተሰባስበው መጽሐፍ
ቅዱስን ከተማማሩ፣ በአንድነትም በመዝሙር በቅኔ ለአምላካቸው ከተቀኙ እንደ ምንፍቅና መታየት ከተጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይሁንም እንጂ
ቅድስት ቤተክርስቲያን፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቀዳሚ ትምህርት መሰረት አድርጋ ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ በየትኛውም ሥፍራ
መሰበክ እንዳለበት ታስተምራለች፡-
·
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፡፡” ማቴ 28፡-19፡፡
ደቀመዝሙሩና ከእርሱ ጋር የታሰሩ ወገኖች፥ ይሄንን የሐሰት ክስ ያቀነባበሩባቸውን ግለሰቦች መልሳችሁ መክሰስ ትችላላችሁ
ቢባሉም እንኳ “በቀል የእግዚአብሔር ነው” በማለትና “ከአባታችን ከእግዚአብሔር የተማርነው
ይቅርታና ምህረት ማድረግ ነው” በማለት አንዳችም አጸፋ ለማድረስ
እንዳልፈለጉ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ይሄ ደግሞ የአሰበ ተፈሪ ሐገረ ስብከት ሠራተኞችን ትዝብት ውስጥ የሚጥልና በቤተክርስቲያንም
ወንጌል ለምን ተማማራችሁ በማለት የሚያሳስርና የሚከስ አባት የላትም፡፡ ይህንን ያደረጉት “የገባውን እውነት ቀብሮ ልጆቼን
በምን አሳድጋለሁ ብሎ በግልጽ ወንጌልን የሚቃወመው ላዕከ ወንጌል
ምንዳ ጉታ፥ ትዳሩን ባለማክበር በምንዝርና የሚታወቀው ሊቀ ብርሃናት ካህሊ በቃሉ፥ እና “የሴት አሳዳጁ” በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው መልአከ
ጸሐይ ዮሐንስ ቀሲስ የማታ ወርቅ” በተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች በዓመጻ ተነሳስተው ከማህበሩ በሚያገኙት
የአልኮል ቅምሻ ተታለው መሆኑን ታውቋል፡፡
“ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን” እንዲል መጽሐፍ ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር
ብቻ ይሁን! አሜን!
Diyakon Kefyalew tufa, Tebarek. betechaleh meten gin Tibeb metekem endtchel emekrhalehu. tsega yebzaleh.
ReplyDelete